የሩሲያው ፕሬዘዳንት ብላድሚር ፑቲን ለፊንላንዱ አቻቸው ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ የቃልኪዳን አባል ሃገራት ኔቶን ከተቀላቀለች ስህተት እንደሚሆን መናገራቸውን ከክሬምሊን የወጣ መግለጫ አስታውቋል።
የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ትላንት በስልክ ተገናኝተው ተነጋግረዋል። በሌላ በኩል በተመሳሳይ ሰዓት የዩናይትድ ስቴትስ የአናሳዎች መሪ ሚች ማኮኔል የሪፐብሊካን ልዑክን እየመሩ በዩክሬን ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ቮልደሚየር ዘለንስኪ ይሄ ጉብኝት አሜሪካ ዩክሬንን ለመደገፍ ያላትን ተነሳሽነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በተያያዘ የሩሲያ ወታደሮች ሳምንታት ከዘለቀ የአየር ድብደባ በኋላ ከዩክሬኗ የሰሜን ምስራቅ ከተማ ካርኪቭ ለቀው በመውጣት ላይ ይገኛሉ።