በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀማቸውን ክልሉ አመነ


የሶማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀማቸውን ክልሉ አመነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:35 0:00

የሶማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀማቸውን ክልሉ አመነ

የፀጥታ አካላት እና የታጠቁ ኃይሎቹ ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ በመጠቀም 11 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል በትንሹ 33 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል በሚል በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት የቀረበበት የሶማሌ ክልል ድርጊቱ መፈፀሙን አመነ።

የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሒም ኦስማን የክልሉ የጸጥታ አካላት ያልተመጣጠነ ኃይል መጠቀማቸውን አረጋግጠዋል።

ይሁንና የድርጊቱ ፈጻሚዎች ለሕግ እንዳልቀረቡ የሚገልፀውን የሪፖርቱን ክፍል አስተባብለዋል። ስህተት “የፖለቲካ አመራሮቹም ሆኑ የጸጥታ ሃይሎች ላይ አስፈላጊው ማጣራት እየተወሰደ ነው” ብለዋል።

ዘገባው የአዲስ ቸኮል ነው።

XS
SM
MD
LG