በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
የዓለም አቀፉ ጥምረት በአፍሪካ እስላማዊ መንግሥትን ለማጥቃት ሁሉገብ ዝግጅት እያደረገ ነው

የዓለም አቀፉ ጥምረት በአፍሪካ እስላማዊ መንግሥትን ለማጥቃት ሁሉገብ ዝግጅት እያደረገ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የናይጄሪያ ወታደሮች እአአ ጥቅምት 12/2019
ፎቶ ፋይል፦ የናይጄሪያ ወታደሮች እአአ ጥቅምት 12/2019

እስላማዊ መንግሥት ቡድን የደቀነው እና የኖረው የሽብርተኝነት አደጋ ሩስያ ዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት ለወራት ቢያጠላበትም አሁን ወደ ዓለም አቀፉ መድረክ ተመልሶ መጥቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ ሽብርተኛ ቡድኑ ሌላ አህጉር አደገኛ የሽብርተኝነት መጫወቻ ሜዳ ከማድረጉ በፊት ይደረስበታል ብላ ተስፋ አድርጋለች።

የ85 አገሮች እና የአረብ ሊግ፣ ኔቶና ኢንተርፖልን ጨምሮ፣ የተወሰኑ ድርጅቶች ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት ሞሮኮ፣ ማራካሽ በሚኒስትሮች ደረጃ ጉባዔ ተቀምጠዋል።

ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ እና “አይሲስን ድል ማድረጊያ ዓለም አቀፍ ቅንጅት” የሚል ስያሜ የተሰጠውን ስብሰባ በጋራ ያዘጋጁት ሞሮኮና ዩናይትድ ስቴትስ ናቸው። የስብሰባው ትኩረት በዓለም ዙሪያ ያሉ የአይሲስ ርዝራዦችን በቀጣይነት ማጣደፍ ስለሚቻልበት መንገድ ለመምከር መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ ያወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ይሁን እንጂ ረቡዕ የሚኒስትሮች ስብሰባው ከመካሄዱ አስቀድሞ በፊት አስተያየታቸውን ለቪኦኤ የሰጡ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን፣ አብዛኛው የስብሰባው ትኩረት፣ በአፍሪካ እስላማዊ መንግሥት ወይም የዓለም አቀፉ ቅንጅት አባላት ዳኢሽ ወይም አይሲስ ብለው የሚጠሩት ቡድን አደጋ ሲያቆጠቁጥ የቆየባት የአፍሪካ አህጉር እንደምትሆን ገልጸዋል።

በዓለም አቀፉ አይሲስን ማሽነፊያ ቅንጅት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ልኡክ ደግ ሆይት የተደቀነው በበከፍተኛ ደረጃ የሚያሳስብ አደጋ ነው የምናወራው በሽዎች ስለሚቆጠሩ ተዋጊዎች ነው ብለዋል፡፡ አስከትለውም

“በጣም የሚያሳስበው በአሁኑ ወቅት ከሰሃራ በታች ባሉ አገሮች የሚንቀሳቀሱት የአይሲስ ቅርንጫፎች ነገር ነው፡፡ በጣም በርካታ ናቸው፡፡ እንደፈለጉ የሚዘዋወሩበት ስፋት ያለው ቦታም አግኝተዋል" ብለዋል፡፡

ምዕራብ አፍሪካ ውስጥ እየተስፋፋ ያለው እንቅስቃሴያቸው

በአንዳንዶቹ የአፍሪካ አካባቢዎች በተለይም ምእራብ አፍሪካ ውስጥ አይኤስ ርእዮተ አለሙ እንኳን ባይሆን ያነገበው አርማው ተከታይ እያገኘ ነው ብለው የዩናይትድ ስቴትስ እና የሌሎችም የም ዕራባውያን ሀገሮች ወታደራዊ እና ጸረ ሽብር ባለሥልጣናት ለበርካታ ዓመታት ሲያስጠነቅቁ በርካታ ባለሥልጣናት እንደሚሉት እና የተባበሩት መንግሥታት የደረሰው የሥለላ መረጃ እንደሚያመለክተው አይኤስ አፍሪካ ውስጥ ካሉት ተባባሪዎች ሁሉ ትልቁ እና ጠንካራው መሰረቱ ናይጄሪያ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው “የምእራብ አፍሪካው አይኤስ” የሚባለው ነው፡፡

የአልቃይዳ ግብረ አበር የሆነውን ቦኮ ሃራምን ከአካባቢው ያባረረው ይህ ቡድን በናይጄሪያ፣ ካሜሩንና ኒጀር፣ እስከ 5ሺ የሚደርሱ ተዋጊዎች እንዳሉት ይገመታል፡፡ ሌላው የአይኤስ ተባባሪ ቡድን “አይኤስ በትልቁ ሰሃራ” የተባለው በቤኒን ጋናና ቶጎ የሚንቀሳቀስ ሲሆን እስከ 1ሺ የሚደርሱ ተዋጊዎች አሉት።

“አይኤስ ሞዛምቢክ” የተባለው ቡድን “አህሉ ሱናዋል ጃመዓ” ከተሰኘው ቡድን ባገኛቸው 1ሺ 200 ተዋጊዎች የተጠናከረ ሲሆን፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ቡድኑ እኤአ በነሀሴ 2020፣ ሞኪምቦዋ ዳ ፓርያ የተሰኘውን ቁልፍ ወደብ፣ ለተወሰነ ጊዜ በቁጥጥር ስር በማዋሉ ባተረፈው ዝና ተበረታትቶ ተጠናክሯል።

አሁን በቅርብ ደግሞ “አይ ኤስ ሞዛምቢክ” ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ባሉት ተባባሪዎቹ አማካይነት የአለም አቀፉን የፋይናንስ ሥርዓት ሊያውክ እንደሚችል ዩናይትድ ስቴትስ ስጋቷን ገልፃለች።

ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በደረሰ ሌላ መረጃ መሰረት ደግሞ ሌሎቹ የአይኤስ ተባባሪዎች ትናንሽ ይሁኑ እንጂ ሶማልያ ውስጥ ግፋ ቢል በመቶዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች ይዘው ይንቀሳቀሳሉ የመንን በመሳሰሉ ሀገሮች ውስጥም ይዋጋሉ። ቡድኑ ሊቢያና ሞሮኮ ውስጥም መንቀሳቀሱን ቀጥሏል። በዚያ ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት ተዋጊዎቹ ከሌሎች ስምንት የአፍሪካ ሀገሮች የሄዱ ናቸው ነው የሚባለው።

ከሊቢያም ሌላ አይኤስ ሊስፋፋ የቻለው በሚንቀሳቅስባቸው ሀገሮች በአገሩ ሰዎች ለመጠቀም ብልጠት የተመላበት ስልት መከተሉን በመቀጠሉ መሆኑን ምእራባውያን ባለስልጣናት ይናገራሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አባል ሆይት ለቪኦኤ ሲናገሩ “አንዳንዶቹን እነዚህን አካባቢዎች ማስተዳደር አስቸጋሪ ነው፣ ይህ ሁኔታ የሚቀየርም አይመስለኝም” ብለዋል።

“አሁን እንደምናየው አይሲስ በየአካባቢው ያሉ ቅሬታዎችን እየተከታተለ በዚያ መሰረት ምልምላዎችን ያካሂዳል። ተመልማዮቹም ወዲያውኑ የትልቁ እስላማዊ መንግሥት ንቅናቄ አካል ይሆናሉ” ብለዋል።

ደግ ሆይት ጨምረው ከየአገሩ ውስጥ እየመለመሉ ተዋጊያቸውም እየተበራከተላቸው ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ታዲያ የሽብርተኛው ቡድን በአፍሪካ መስፋፋት ጉዳይ ትኩረት ማድረግ ሴፈልግ ይህ የመጀመሪያ አይደለም፡፡

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ ሀሳቡን እኤአ ህዳር 2019 ላይ አንስተውት ነበር። ባላፈው ሰኔም፣ ጥምረቱ በዋናነት በወታደራዊ ኃይል ብቻ በመጠቀም ከመተማመን ይልቅ፣ ሁለገብ አቀራረብ መከተል አእስፈላጊ ነው በማለት የአፍሪካ ግብረ ኃይል መቋቋሙን አስታውቋል።

የዩናይትድ ስትቴስ ባለሥልጣናት ወደ ሚኒስትራዊ ጉባዔው ሲያመሩ ወታደራዊ ኃይል፣ ብቻውን ውጤታማነትን ሊያመጣ አይችልም የሚል ጠንካራ አቋም ይዘው ነው።

የስቴት ዲፓርትመንቱ ባለሥልጣን ሆይት “ያሁኑ አቀራረባችን “እንደ ታንክ ያሉ ወታደራዊ መሳሪያዎችን መጠቀም አይሆንም። በማለት በሶሪያና ኢራቅ፣ አይሲስን ድል ለመንሳት ከተከሉት መንገድ የተገኘውን ልምድ እንደሚጠቀሙ አጽንኦት ሰጥተዋል።

“በየትኛውም የአገር ውስጥ ውጊያና ፍጥጫዎች የመሰለው ነገር ውስጥ ተስበን አንገባም። ሲቪላዊ የአቅም ግንባታ ላይ እንሰራለን ያም የድንበር ጸጥታን፣ አሻራዎችን መሰብሰብ መረጃዎችን መለዋወጥ በፍትህ ሂደቶች ላይ ማተኮር” የመሳሰለውን ያካትታል ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በአፍሪካ አዲስ እየተስፋፋ ያለውን አይኤስን ለመመከት የሚያደርጉት አዲስ ጥረት አሁን በአውሮፓ ህብረትና አጋሮቻቸው እንዲሁም ናይጄሪያ ኒጀርና ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ራሳቸው እያደረጓቸው የሚገኙትን ጥረት የሚደግፍ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተውታል።

ትብብርን ማሳደግ

ቤኒን ከወዲሁ ሌሎች 17 የአፍሪካ አገሮች የሚገኙበት ጥምረት ለመቀላቀል ወስናለች። ሌሎችም ጥምረቱን መቀላቀል የሚችሉ ሲሆን ወደ ጥምረቱ መግባት የማይፈልጉ ቢሆን እንኳ መሳተፍ እንደሚችሉ ተመልክቷል።

“አንዳንድጊዜ የቅርብ ተመልካቾችን ወይም በተለያዩ ምክንያቶች የግድ የጥምረቱ አካል መሆን ያልቻሉ፣ ግን ደግሞ ቁልፍ ሚና መጫወት የሚችሉትን እንፈልጋለን”ያሉት፣ በዩናትይድ ስቴትስ አይሲስን ለማሸነፍ የተቋቋመው የዓለም አቀፉ ጥምረት ልዩ ልኡክ ዴክስተር ኢንግራም ናቸው፡፡

“እንደ ሞዛምቢክ ያሉ አገሮችን ተመልክቱ” የሚሉት ኢንግራም “ሞዛምቢክ ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ በደረሰው አደጋ፣ በተለይ የሽብርተኝነት ጥቃት አደጋ ከደረሰባቸው 10 አገሮች አንዷ ናት፡፡ ግን የጥምረቱ አባል አይደሉም ባይሆኑም እነሱን ለማነጋገር እና አፍሪካ ላይ በሚያተኩሩ ስብሰባዎቻችን ላይ እንዲሳተፉ እንፈልጋለን በጠረጴዛው መቀመጫ ተዘጋጅቶላቸዋል” ብለዋል።

ኢንግራም እንደሚሉት፣ በተለይ የአፍሪካ ሀገሮች እንዲሳተፉ ለመቀስቀስ ጸረ አይሲስ እንቅስቃሴ ሁል ጊዜም ከባድ እርምጃ ይጠይቃል ማለት እንዳልሆነ እና አንዳንዴም አስቀድሞ ያለው አቅም መጠቀም በቂ ሊሆን እንደሚችል ማሳወቅ ይጠቅማል ብለዋል፡፡

“እኛ ማድረግ የምንፈልገው በየቦታው የተሰበሰቡ መረጃዎች ወስደን እነሱን ገጣጥሞ መመልከት ነው። ከአንድ ቦታ የምናገኘው የጣት አሻራ ኢራቅ ወይም ሞዛምቢክ፣ ወይም ማሊ ውስጥ ቦምብ ቢፈነዳ እና በዚያ ፍንዳታ ላይ ከሚሰበሰብ አሻራ ጋር ያ ደግሞ ብሪታኒያ ወይም ፕራግ ውስጥ ያለ ታክሲ ነጂ ጋ ከወሰደን ድል ማለት እሱ ነው” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG