በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ሚዲያ ተጨማሪ ፈተናዎች


የኢትዮጵያ ሚዲያ ተጨማሪ ፈተናዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:31 0:00

በፖለቲካ፣ በአፋኝ ህጎች በመረጃ ማግኘት እና ከገቢ ጋር በተያያዙ ችግሮች ታጥሮ የኖረው የጋዜጠኝነት ሙያ ቀደም ሲል ከመንግስት ሲደርስበት ከቆየው ጫና በተጨማሪ ባልታወቁ ግለሰቦች እና ቡድኖች ለሚደርስ ጥቃት ተጋልጧል። ከማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ጋር ተያይዞም ፈተናዎችም በርትተውበታል። በነዚህና ተያያዥ የኢትዮጵያ ሚዲያ ወቅታዊ ውጣ ውረዶች ዙሪያ በዩናይትድ ስቴትስ የሚሲሲፒ ዩንቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑትን ዶክተር ዘነበ በየነን አነጋግረናቸዋል።

በኢትዮጵያ ከአመት አመት በፖለቲካ፣ በአፋኝ ህጎች በመረጃ ማግኘት እና ከገቢ ጋር በተያያዙ ችግሮች ታጥሮ የኖረው የጋዜጠኝነት ሙያ ቀደም ሲል ከመንግስት እና አፋኝ ህጎች ሲደርስበት ከቆየው ጫና በተጨማሪ ባልታወቁ ግለሰቦች እና ቡድኖች ለሚደርስ ጥቃት ተጋልጧል። ከማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ፈተናዎችም በርትተውበታል። በነዚህና ተያያዥ የኢትዮጵያ ሚዲያ ወቅታዊ ውጣ ውረዶች ዙሪያ ያናገርናቸው ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የሚሲሲፒ ዩንቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መምህር እና ዓለም አቀፍ ፕሮግራሞች አስተባባሪ ዶክተር ዘነበ በየነ በአንድ ሀገር ውስጥ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ሚዲያ ቀዳሚው ገፈት ቀማሽ ነው ይላሉ።

ማህበራዊው ሚዲያ የጥቅሙን ያክል ጉዳቱም እያመዘነ መሆኑን የሚያሰምሩበት ዶክተር ዘነበ በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው መንግስት ጋዜጠኞችን የማሰር ሂደትም በኢትዮጵያ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ እንደማይሆኑ በመግለፅ የመናገር ነፃነት በሀላፊነት መተግበር የሚችልበት መንገድ ላይ ማተኮር እንደሚገባ ያስረዳሉ።
XS
SM
MD
LG