በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካሜሩን አለም አቀፉ የቀይመስቀል ቀን የሰራተኞች ደህንነትን በማሰብ ተከበረ


የቀይ መስቀል ሰራተኞች የማዕከላዊ አፍሪካ ፍልሰተኞችን ወደ ጋዶ ካሜሩን እየወሰዱ
የቀይ መስቀል ሰራተኞች የማዕከላዊ አፍሪካ ፍልሰተኞችን ወደ ጋዶ ካሜሩን እየወሰዱ

በዛሬው ዕለት ታስቦ የዋለውን አለም ዓቀፉን የቀይ መስቀል ቀን፤ በካሜሩን በመቶዎች የሚቆጠሩ የተቋሙ ሰራተኞች በማዕከላዊ አፍሪካ ያሉ ማኅበረሰቦች ጥበቃ እንዲደረግላቸው በመጠየቅ ተንቀሳቅሰዋል።

ምንም እንኳን እስካሁን ድረስ የተመዘገበ ሞት ባይኖርም የአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ሰራተኞች ለድብደባ እና ለቦኮ ሃራም የሽብር ጥቃት የተጋለጡ መሆናቸውን የረድዔት ሰራተኞች ይናገራሉ።

የካሜሩን መንግስት በማዕከላዊ አፍሪካ ግዛት ውስጥ የቀይ መስቀል ሰራተኞች ከፍተኛ ሚና አላቸው ያለ ሲሆን፤ በአካባቢው በተገንጣዮች ሳቢያ በተፈጠረ ቀውስ ሳቢያ በሽሽት ላይ የሚገኙ 750000 ሰዎች ድጋፍ ማድረጋቸውንም አስታውቋል።

የአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ሰራተኞች በናይጄሪያ፣ ቻድ እና ካሜሩን በቦኮሃራም ሽብር ከቀያቸው ተፈናቅለው በሽሽት ላይ ያሉ ሶስት ሚሊየን ሰዎችን አግዘዋል።

XS
SM
MD
LG