በዌስተርን ዩኒየን ፋውንዴሽን ድጋፍ በየአመቱ በካናዳ የሚዘጋጀው የምርጥ ስደተኞች ሽልማት ዘንድሮ በሰኔ ወር ላይ ለ14ኛ ግዜ ይካሄዳል። ሽልማቱ በስደት ወደ ካናዳ ሄደው ለስኬት የበቁ እና ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ድምፅ መሆን ለቻሉ ሰዎች የተዘጋጀ ሲሆን ዘንድሮ እጩ ሆነው ከቀረቡ 25 ሰዎች መሃከል አንዷ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ መሰረት ሀይለየሱስ ናት። ለ10 አመታት በካናዳ የኖረችው መሰረት ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ፍትህ እንዲያገኙና ራሳቸውን እንዲችሉ የሚንቀሳቀስ Canadian Centre for Women's Empowerment የተሰኘ ተቋም ስራ አስኪያጅ ስትሆን በጤና አገልግሎት ተደራሽነት ዙሪያም ትሰራለች። እ.አ.አ በ2016 ካናዳ የተሻለ ሀገር እንድትሆን ካደረጉ 150 ሴቶች መሃል አንዷ ሆና ተመርጣ የነበር ሲሆን ባለፈው አመት በካናዳ ከአርባ አመት እድሜ በታች ሆነው ስኬታማ መሆን ከቻሉ 40 ሰዎች መሃል አንዷ መሆንም ችላለች። በተጨማሪም ባለፈው አመት ከካናዳ የፓርላማ አባልና የኢኮኖሚ ልማት፣ ስራ ፈጠራ እና ንግድ ሚኒስቴር እጅ ብሄራዊ ሽልማት አግኝታለች። ስመኝሽ የቆየ መሰረት በምትሰራቸው ማህበራዊ እና ፍትሃዊ ንቅናቄዎች ዙሪያ አናግራታለች፣ቀጥሎ ይቀርባል።
"እርግዝና የሞት ፍርድ መሆን የለበትም" መሰረት ሀይለየሱስ፣ የምርጥ ስደተኛ ሽልማት እጩ
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ሜይ 29, 2023
በማዳበሪያ እጥረት የተቆጡ አርሶ አደሮች አቤቱታ
-
ሜይ 29, 2023
በታዳጊው መርከብ 600 ፍልሰተኞች ከሥጥመት ተረፉ
-
ሜይ 29, 2023
ከዘጠኝ ዓመት በፊት የተጠለፉት የቺቦክ ልጃገረዶች አሁንም አልተለቀቁም
-
ሜይ 29, 2023
አሳሳቢው የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ በዩናይትድ ስቴትስ