በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካው ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 443 ደረሰ


ፎቶ ፋይል ጎርፍ ባጥለቀለቃት የደቡብ አፍሪካ ከተማ ደርበን በፅዳት ስራ የተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች/ደርባን እአአ አፕሪል 16/ 2022
ፎቶ ፋይል ጎርፍ ባጥለቀለቃት የደቡብ አፍሪካ ከተማ ደርበን በፅዳት ስራ የተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች/ደርባን እአአ አፕሪል 16/ 2022

የደቡብ አፍሪካን ምስራቃዊ የህንድ ውቂያኖስ ጠረፍ አካባቢ ባጥለቀለቀው ከባድ ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 443 መድረሱ ተዘግቧል። ከሞቱት ሰዎች መካከል የርዳታ ሰራተኞችም ያሉባቸው መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣን ገልጸዋል።

የክዋዙሉ ናታል ክፍለ ሀገር ዋና ሚኒስትር ሲህሌ ዚካካላ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል እንዳስታወቁት እስካሁን የደረሱበት ያልታወቀ ስድሳ ሶስት ሰዎች አሉ።

በጎርፉ በተጎዳው አካባቢቀደም ብሎ የነበረው ዝናባማ የአየር ሁኔታ አስቸግሮ ነበር ያሉት ባለስልጣኑ አሁን ዝናቡ ቀለል ብሎ የርዳታ ሰራተኞች እንደልብ ለመንቀሳቀስ ችለዋል ብለዋል።

በሳምንቱ መጀመሪያ የጠረፏን ደርባን ከተማን እና አካባቢውን ያጥለቀለቀው ጎርፍ መንገዶችን እና ሆስፒታሎችን ያወደመ ሲሆን መኖሪያ ቤቶችንም መውጫ ካጡት ነዋሪዎች ጋር ወስዷል።

እስከመጪው ረቡዕ በሚኖረው ጊዜ ዝናቡ ሙሉ በሙሉ እንደሚቆም ነው የሀገሪቱ የአየር ሁኔታ አገልግሎት ባለስልጣን ፑሴሌቶ ሞፎኬንግ የተናገሩት።

ደርባን ትልቅ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ማእከል ስትሆን ህንድ ውቂያኖስ ዳርቻ የምትገኘው ከተማ ለወትሮው በዚህ የፈረንጆች የእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዐል ብዛት ያለው ጎብኚ የምትስብ መሆኗ ይታወቃል። ትናንት ቅዳሜ ሌሊት ላይ ዝናብ የጣለ ሲሆን አሁን ግን ዝናቡ እንዳቆመ ተገልጿል።

ዛሬ በከተማዋ ዙሪያ ባሉ አብያተ ክርስትያናት እና ሜዳ ላይ ለትንሳኤ በዐል ቅዳሴ የታደሙት ነዋሪዎች በጎርፉ ለተጎዱ ሰዎች ፀልየዋል።

በሞት በተለዩት የደቡብ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ ዴዝመንድ ቱቱ እግር የተተኩት የኬፕታውን ሊቀጳጳስ ታቦ ማክጎባ ደርበንን ጎብኝተው ሲመለሱ በሰጡት ቃል "በጎርፍ አደጋው ማህበረሰቡ እጅግ ከባድ ጉዳት እና ሃዘን ላይ ነው" ብለዋል።

በጎርፉ ምክንያት ከአርባ ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ካለመጠጊያ ቀርተዋልየደቡብ አፍሪካ መንግሥት በጎርፉ ለተጎዱት ሰዎች አስቸኳይ ርዳታ የሚውል ስድሳ ስምንት ሚሊዮን ዶላር መድቧል።

XS
SM
MD
LG