በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሊቢያ አቅራቢያ በተገለበጠው ጀልባ ውስጡ የነበሩ 35 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተ.መ.ድ አስታወቀ

ፎቶ ፋይል - እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር መጋቢት 5/2022 ከአደጋ የተረፉ አፍሪካዊያን ስደተኞች ሊቢያ አቅራቢያ ከሜዲተራኒያ ባህር ላይ
ፎቶ ፋይል - እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር መጋቢት 5/2022 ከአደጋ የተረፉ አፍሪካዊያን ስደተኞች ሊቢያ አቅራቢያ ከሜዲተራኒያ ባህር ላይ

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ዛሬ እንዳስታወቀው የጀልባ አደጋው የተከሰተው ትላንት በምዕራብ ሊቢያ በኩል፣ ሳባርታ በተባለች ከተማ አቅራቢያ ነው። እስካሁን የስድስት ስደተኞችን አስክሬን ማውጣት የተቻለ ሲሆን መገኘት ያልቻሉት 29 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገምቷል።

አደጋው የተሻለ ህይወት ፍለጋ ስደተኞች ከሰሜን አፍሪካ ወደ አውሮፓ በሚያደርጉት ጉዞ በተደጋጋሚ የሚያጋጥም ሲሆን ከአፍሪካ እና መካከለኛው እስያ ጦርነት እና ድህነንት የሚሸሹ ስደተኞች ሊቢያን እንደመሸጋገሪያ ይጠቀሙባታል።

XS
SM
MD
LG