በሱዳን አቢዬ በተባለው ልዩ አስተዳደር አካባቢ የታጠቁ ዘላኖች አደረሱት በተባለውና 41 ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት ላይምርመራ እንዲካሄድ የሱዳን ወታደራዊ መሪ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ግድያው በሱዳን እና ደቡብ ሱዳን መካከልበተፈጠረ የድምበር አለመግባባት እየተባባሰ የመጣው ግጭት አካል መሆኑ ተገልጿል።
ጀነራል አብድል ፈታህ አልቡርሃንሐሙስ እለት ከፍተኛ የጦር አመራሮችን፣ ፖሊስ እና መርማሪዎችን ያቀፈ ሰባት አባላት ያሉት ቡድን እንዲቋቋም ትዕዛዝ አስተላልፈው የነበር ሲሆን አንድ አመት ያስቆጠረውን ግጭት ከስር መሰረቱይመረምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በአቢዬ አስተዳደር የሚኖሩት አብዛኞቹ ሰዎች ደቡብ ሱዳናዊ የዲንቃ ተወላጆችሲሆኑ፣ ሱዳናዊ የአረብ ሚስርያ አርብቶ አደሮችም አልፎ አልፎ ይኖሩበታል።
የሱዳን ሚስርያ ዋና አዛዥ ሙክታር ባቦ ንሚር የማህበረሰቡ አባላት አቢዬ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን አምነው፣ራሳቸውን ለመከላከል የወሰዱት ርምጃ ነው ብለዋል።