ሩሲያ - የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቦሪስ ጆንሰን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሊዝ ትረስ እና መከላከያ ሚኒስትሩን ቤንዋላስን እንዲሁም ሌሎች አስር የእንግሊዝ መንግስት አባላትና ፖለቲከኞች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ማገዷን የራሽያ የውጭጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።
ሩሲያ ውሳኔውን ያስተላለፈቸው የእንግሊዝ መንግስት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ ባሳየችው ጠብ ጫሪነት እናበከፍተኛ የሩሲያ ባለስልጣናት ላይ በጣለችው ማዕቀብ ምክንያት መሆኑን፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መግለጫአመልክቷል።
ክሬምሊን ለዩክሬን ጠንካራ ድጋፍ ያሳዩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆንሰንን "ጸረ ሩሲያ ለመሆን በሚደረገው ሩጫ ዋናተሳታፊ" ስትል ገልፃቸዋለች።
ጆንሰን ከሳምንት በፊት ኪየቭ በመገኘት ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቩለድሚር ዚለንስኪ ጋር ተገናኝተው የነበረ ሲሆን ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ ሁለቱ ሀገራት ላላቸው ትብብር ተመሰጋግነዋል።