በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ፣ ሁለተኛ ምዕራፍ የናይል ምድብ ጨዋታዎች ተጀመሩ


የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ፣ ሁለተኛ ምዕራፍ የናይል ምድብ ጨዋታዎች ተጀመሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:00 0:00

የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ፣ ሁለተኛ ምዕራፍ የናይል ምድብ ጨዋታዎች ተጀመሩ

የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ፣ ሁለተኛ ምዕራፍ የናይል ምድብ ጨዋታዎች ቀጥለዋል። በግብጽ ካይሮ በመደረግ ላይ ባሉት ግጥሚያዎች ከስድስት ሀገራት የመጡ ክለቦች የምድቡ የበላይ ለመሆን ይፎካከራሉ።

ከዚህ ምድብ የሚመረጡት ሦስት ክለቦች በርዋንዳ ኪጋሊ በሚደረጉት የፍጻሜው ምዕራፍ ተሳታፊ ይሆናሉ።

በናይል ምድብ ውስጥ የተደለደሉት ክለቦች የግብጹ ዛማሌክ፣ የአንጎላው ሲኤፒ ደ ሉዋንዳ፣ የማሊው ኤፍኤፒ(የፖሊስ ሰራዊት ክለብ)፣ የደቡብ ሱዳኑ ኮብራ፣ የኮንጎው ቢሲ ኢስፖይር ፉካሽ፣ የደቡብ አፍሪካው ኬፕ ታውን ታይገርስ ክለብ ናቸው።

ከባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በተደረጉ ጨዋታዎች ድል ያደረገው የአንጎላው ሲኤፒ ደ ሉዋንዳ ምድቡን እየመራ ይገኛል። ቡድኑ ትናንት ባደረገው ጨዋተ የደቡብ አፍሪካውን ኬፕታውን ታይገርስን 90 ለ 61 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የግብጹ ዛማሌክ እና የማሊው ኤፍኤፒ በነጥብ ልዩነት በሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ዛሬ አመሻሹን በዶ/ር ሀሰን ሙስጠፋ የስፖርት ማዕከል የግብጹ ዛማሌክ እና የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ታይገርስ እንዲሁም የደቡብ ሱዳኑ ኮብራ ከ ኮንጎ ኢስፖየር ፉካሽ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

የአፍሪካ የቅርጫት ኳስ ሊግ ቀደም ባሉት ሳምንታት በሴኔጋል ዳካር፣ የሳህራ ምድብ ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በምድቡ ያየሉ አራት ሀገራት ከናይል ምድብ አሸናፊዎች ጋር በጎረጎሳዊያኑ ግንቦት አጋማሽ በኪጋሊ የስፖርት ማዕከል ይገናኛሉ።

XS
SM
MD
LG