በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን አዲስ ጥቃት ከፈተች


ሩሲያ በዩክሬን ያካሄደችውን ወረራ ተከትሎ ሚያዚያ 10, 2022 ኒፕሮ ከተሰኘው አውሮፕላን ማረፊያ የሚነሳ ጭስ ታይቷል። 
ሩሲያ በዩክሬን ያካሄደችውን ወረራ ተከትሎ ሚያዚያ 10, 2022 ኒፕሮ ከተሰኘው አውሮፕላን ማረፊያ የሚነሳ ጭስ ታይቷል። 

ሩሲያ ዛሬ በምስራቅ ዩክሬን ባካሄደችው የአየር ጥቃት ትምህርት ቤቶችና የመኖሪያ ህንፃዎችን መደብደቧን የሉሃንስክ ክልል ባለስልጣናት አስታወቁ። ጥቃቱ ትላንት መጀመሩን ተከትሎ ነዋሪዎች አካባቢውን አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቀው ነበር።

ሆኖም የራሽያ ሚሳይል አርብ እለት ክራማቶርስክ የሚገኝ የባቡር ጣቢያ ላይ ጉዳት አድርሶ 52 ሰዎች ከተገደሉ በኃላ ዩክሬናዊያን አካባቢያቸውን ለመልቀቅ ፍርሃት አድሮባቸዋል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሰራዊታቸው በሰሜን እና ምዕራብ ኪየቭ ከፍተኛ መከላከል ከገጠማቸው እና አካባቢውን ለቀው ከወጡ በኃላ ወረራውን ወደ ምስራቅ ዩክሬን መቀየራቸውን ወታደራዊ ተንታኞች ገልፀዋል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዚለንስኪ ትላንት ሲ ቢ ኤስ ከተሰኘው የዩናይትድ ስቴትስ የቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የሩሲያ ወረራ በዩክሬን ብቻ የሚገታ አይደለም ወይም በኛ ነፃነት እና ህይወት ውድመት ብቻ አይቆምም። መላው አውሮፓ የሩሲያ ኢላማ ነው" ሲሉ አስጠንቀዋል።

XS
SM
MD
LG