የኢራን ምክር ቤት አባላት እ.አ.አ በ2015 ተደርሶ የነበረውና የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ዋስትና የሰጠው የኒውክሌር ስምምነት በድጋሚ እንዲያንሰራራ የሚያስችሉ ቅደመ ሁኔታዎችን ማውጣታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የኢራን ምክርቤት አባላት ባወጡት መግለጫም፣ ዩናይትድ ስቴትስ ዳግም ስምምነቱን ጥላ እንደማትወጣ በምክርቤቷ የፀደቀ ማስተማመመኛ እንድትሰጥ እና፣ በኢራን ላይ ማዕቀቦች እንዳይጣሉ ጠይቀዋል።
እ.አ.አ በ2018 የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኒውክለር ስምምነቱን ካቋረጡ በኃላ ኢራን ከስምነቱ ውጭ የኒውክለር ፕሮግራሟን በማሳደጓ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን የ2015ቱን ስምምነቱን ዳግም ተግባራዊ በማደርግ ጉዳይ ላይ፣ ላለፈው አንድ አመት በቪየና ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት ሲያካሂዱ ቆይተዋል።
ሆኖም ታህራን እና ዋሽንግተን እልባት ባላገኙ ጉዳዮች ላይ ፖለቲካዊ ውሳኔ ማሳለፍ ባለመቻል እርስ በእርስ መወነጃጀል በመቀጠላቸው በሁለቱ ሀገራት መሃክል የሚደረገው ድርድር መራመድ ሳይችል መቆሙን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።