በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤልና ፍስልጤማውያን ግጭት አገርሽቷል


የእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች በቴል አቪቭ ጥቃቱ የደረሰበትን አካባቢ ሲያስሱ እኤአ ሚያዝያ 7/2020
የእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች በቴል አቪቭ ጥቃቱ የደረሰበትን አካባቢ ሲያስሱ እኤአ ሚያዝያ 7/2020

አንድ ፍልስጤማዊ ታጣቂ ባላፈው ሀሙስ ምሽት በእስራኤል ቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኝ ታዋቂ የምሽት ክለብ በመሄድ ባደረሰው ጥቃት ሶስት እስራኤላውያን ወጣቶችን ሲገድል በርካቶችን አቁስሏል፡፡

የእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች አጸፋውን ለመመለስ ዛሬ ቅዳሜ በምዕራብ ጋዛ ዳርቻ በምትገኝ የጄኒን ከተማ ጥቃት ፈጽመው አንድ ፍልስጤማዊ ሲሞት 12 ደግሞ መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡

በምሽት ክለቡ ላይ የተካሄደውን ጥቃት ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፋታሊ ቤነት በሰጡት መግለጫ ከላፈው መጋቢት ወር ጀምሮ እየጨመረ የመጣውን የሽብር ጥቃት እንዲያበቃ ለማድረግ ጸጥታ ኃይሎች ለሚወስዱት የዘመቻ እምርጃ “ሙሉ ነጻነት” የሰጧቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“ይህ ጦርነት እንዲያበቃ ምንም ገደብ የለም፣ አይኖርምም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የእስራኤል ጸጥታ ኃይሎች ዛሬ ቅዳሜ በጄኒኒ ከተማ በሚገኙ የፍልስጤማዊያን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያና አካባቢው ላይ የአሰሳ ዘመቻውን መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡

በዛሬው ጥቃት የተገደለውን የ25 ዓመት ወጣት ፍልስጤማዊ አህመድ አል ሰዐዲ አስክሬንና የጋዛ አካባቢ እስላማዊ ሚሊሻ ቡድን ሰንደቅ ዐላማ የያዙ በርካታ ፍልስጤማውያን በጎዳናዎች ላይ በዝተው መታየታቸው ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG