በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ጋር ተነጋገሩ


ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በትናንትናው እለት ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራሞፎሳ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ዋይት ሀውስ ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

መሪዎቹ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ማሻሻልና የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በጋራ መከላከልን ጨምሮ፣ በሩሲያው የዩክሬን ወረራ ዙሪያ መነጋገራቸውም ተመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን በተለይ ለሩሲያው የዩክሬን ወረራ ግልጽና ወጥነት ያለው ዓለም አቀፋዊ ምላሽ የሚያስፈልገው መሆኑን አጽን ኦት መስጠታቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡

ሁለቱ መሪዎች በዩክሬን ስለደረሰው ሰብአዊ ቀውስ ስለ ሸቀጦች ዋጋና የአቅርቦት መስመሮች እንዲሁም ስለ አፍሪካ የምግብ ደህንነት ዋስትና መነጋገራቸው በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

XS
SM
MD
LG