No media source currently available
"ሙዚቃዊ " የተሰኘ የአዳዲስ ሙዚቀኞችን ስራ በዲጂታሉ ዓለም ለማስፋፋት የወጠነ አውታር ከሰሞኑ በይፋ ስራ ጀምሯል። ላለፉት ሁለት ዓመታት በማህበራዊ መገናኛ አውታሮች ላይ የቤት ውስጥ ኮንሰርቶችን በማቅረብ ዕውቅናን ያገኘው ተቋም ፣ በቅርቡ የአዳዲስ ወጣቶችን ስራ ማሳተም፣ ዕድል ያላገኙ የብሄረሰብ ሙዚቃዎችን ከአድማጭ ማስተዋወቅ የመሰሉ መርሐ ግብሮችን ጀምሯል። የመርሀ-ግብሩ ግብር ኃላፊ አቶ ሲሳይ መንግስቴ ጋር የተደረገውን ቆይታ ይከታተሉ።