በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን ከነጻነቷ ወዲህ አስከፊ የሆነውን እርሃብ እየተጋፈጠች ትገኛለች


በደቡብ ሱዳን ከተ.መ.ድ የዓለም የምግብ መርሃግብር የምግብ ድጋፍ ለመቀበል የተሰለፉ ሴቶች
በደቡብ ሱዳን ከተ.መ.ድ የዓለም የምግብ መርሃግብር የምግብ ድጋፍ ለመቀበል የተሰለፉ ሴቶች

ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ከተቀዳጀች ከ10 ዓመት በኋላ ሃገሪቱ በግጭት እየታመሰች፣ በተለያዩ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎ ውስጥ በማለፍ ዜጎቿን መመገብ አዳግቷት ትገኛለች፡፡ በአንድ ወቅት የደስታ እና የተስፋ ስሜት ፈጥሮ የነበረው ነጻነቷም ስሜት የከሰመ ይመስላል፡፡

በደቡብ ሱዳን የተ.መ.ድ የሰብዓዊ አስተባባሪ የሆኑት ሳራ ባይሶሎው ንያንቲ ከዓመት ወደ አመት ሰዎች ከመከራ ለመውጣት ቢታገሉም ተጨማሪ ድህነት እና ተስፋ መቁረጦች እየተፈታተኗቸው ይገኛሉ ብለዋል፡፡

አስተባባሪዋ “በደቡብ ሱዳን የሰብዓዊ አቅርቦት ፍላጎትን ለሟሟላት እስከ 1.7 ቢሊየን ዶላር ብንፈልግም ለሰላም ግንባታ። ለማህበራዊ ትብብር እና ለመልሶ ማቋቋም ተጨማሪ ድጋፍ እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡ በተጨማሪም “ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ሰብዓዊ ድጋፍ ብቻውን ችግራቸውን አይቀርፈውም የተጋለጡትንም መርዳታችንን እያረጋገጥን የአቅም ግንባታ ላይ መስራት አለብን” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG