በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአቶ ገላሳ ዲልቦ የቀብር ስርዓት ዛሬ ተፈጸመ


Former OLF Chair person Gelassa Dilbo Funeral
Former OLF Chair person Gelassa Dilbo Funeral

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ( ኦነግ ) የቀድሞ ሊቀመንበር የአቶ ገላሳ ዲልቦ የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል ።

በትጥቅ እና በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ለ45 ዓመታት የቆዩት አቶ ገላሳ ዲልቦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የኢንዱስትሪና የማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ሆነው እያገለገሉ ነበር።

መጋቢት 21/2014 ዓ.ም. ሌሊት ያረፉት አቶ ገላሳ ዲልቦ የቀብር ሥነ ስርዓት ላይ የቀድሞ ባልደረቦቻቸው ፣የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ታዋቂ ግለሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ዛሬ መጋቢት 24 2014 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መካነ መቃብር ተፈጽሟል።

XS
SM
MD
LG