የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጎተሬዥ ትናንት ቅዳሜ በሰጡት መግለጫ በየመን ሁቲ አማጽያንና የሳኡዲ መር ጦር መካከል የሚደረገውን የጥቃት ልውውጥ በማውገዝ እንዲቆም አሳስበዋል፡፡
አማጽያኑ በጅዳ አቅራቢያ በሳኡዲ የነዳጅ ማምረቻ ተቋማት ላይ ባላፈው ዓርብ ጥቃት አድርሰዋል፡፡
በሳኡዲ አረብያ የሚመራው የጥምረት ጦርም በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ እና የሰአብዊ እርዳታ አቅርቦት መግቢያ በሆነችው በሆዲዳ የወደብ ከተማ ባለፈው ቅዳሜ የአውሮፕላን ድብደባ አካሂዷል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቀው በድብደባው 8 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፡፡
እኤአ 2014 በኢራን የሚመራውን የሁቲ ጦር ሰነዓን መቆጣጠሩን ተከትሎ በሳኡዲ አረብያ የሚመራው ጦር ጣልቃ በመግባት የየመንን መንግስት መደገፍ ከጀመረ ሰባተኛው ዓመቱን መያዙ ተነገሯል፡፡