በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ፕሬዚዳንት ፑቲን በሥልጣን መቆየት አይችሉም አሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳን በፖላንድ ዋርሶ እኤአ መጋቢት 26
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳን በፖላንድ ዋርሶ እኤአ መጋቢት 26

ትናንት ቅዳሜ የአውሮፓ ጉዟቸውን ያጠናቀቁት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ በፖላንድ ከተማ ዋርሶ ባሰሙት ንግግራቸው፣ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን “በሥልጣን ሊቆዩ አይችሉም” ብለው ተናገሩ፡፡

ባይደን በሩሲያ አንዲትም ስንዝር የኔቶ አባላትን ግዛት እንደማያስነኩም ቃል ገብተዋል፡፡

“የኔቶ አባል አገራትን ግዛትና ድንበር ለማስጠበቅ በስምምነት አንቀጽ 5 መሠረት የገባነው የተቀደሰ ቃል ኪዳንና ግዴታ አለብን” ያሉት ባይደን ፑቲን ከዚያች የኔቶ አገራት ድንበር “አንዲት ስንዝር አልፋለሁ ብለው እንዳያስቡ” በመግለጽ አስጠንቅቀዋል፡፡

ዩክሬናውያን አገራቸውን ለማዳን፣ ዴሞክራሲያቸውንና ነጻነታቸውን ለማስጠበቅ እየተፋለሙ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ባይደን ዩክሬናውያን በጀግንነት እየመከቱ ካሉት ውስጥ “ትልቁን ስፍራ የሚይዘው የሁሉም ሰዎች መሠረታዊ መርህ የሆነውን ዴሞክራሲን ነው” ብለዋል፡፡

“ዩክሬን ለሩሲያ ድል አትሆንም፣ ነጻ ሰዎች ጨላማና ተስፋ የሌለው ህይወት መኖሩ አይፈልጉም ሲሉም” ተናግረዋል፡፡

ዋይት ሀውስ ፕሬዚዳንት ባይደን ፑትን በሥልጣን አይቆዩም ሲሉ የአገዛዝ ለውጥ እናደርጋለን ማለታቸው አለመሆኑን ገልጿል፡፡

ክሬምሊን የባይደንን ንግግር አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ "መሪውን መምረጥ ያለበት የሩሲያ ህዝብ ነው" ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG