የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ 'በኢትዮጵያ ሰላምና ዲሞክራሲን እንዲሰፍንለማበረታታት' በሚል ርዕስ በኮሚቴው ሊቀመንበር ሴናተር ሮበርት ሜንዴዝ በቀረበው S. 3199 የተሰኘ ረቂቅ ህግ ዙሪያምስክሮችን ለመስማት ዛሬ ቀነ ቀጠሮ ይዞ ነበር። ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ያሉትን ችግሮች ለመፍታትአሜሪካና ኢትዮጵያ በተሻለ መግባባት እየሰሩ ባለበት ወቅት ረቂቅ ህጉ ለውይይት መቅረቡ ጥረቱን እንደሚያደናቅፍናየሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት እንደሚጎዳ ሲገልፅ፣ ጉዳዩን የሚከታተሉ ሌሎች አካላት ደግሞ ህጉ ቢፀድቅ ኢትዮጵያ ወደሰላም እና ዲሞክራሲ እንድትሄድ የሚገፋፋ ነው በማለት ድጋፋቸውን ገልፀዋል። ስመኝሽ የቆየ ዝርዝር አላት።
በዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር በሆኑት ሴናተር ሮበርት ሜንዴዝ እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር ባለፈው አመት ህዳር ወር ላይ የቀረበውና በሴናተ ጄምስ ሪሽ እና ሴናተር ክሪስ ኩንስየተደገፈው 'በኢትዮጵያ ሰላምና ዲሞክራሲ ለማበረታታት' በሚል ርዕስ ቀርቦ ለዛሬ ምስክሮችን ለመስማት ቀነ ቀጠሮየተያዘለት S. 3199 ረቅቅ ህግ - ኢትዮጵያ ችግሮቿን ለመፍታት እየተንቀሳቀሰች ባለችበት ወቅት መቅረቡ አግባብአይደለም በማለት ረቂቅ ህጉ እንዲነሳ መጠየቃቸውን በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍፁም አረጋለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በደቡብ ካሮላይና የህክምና ዩንቨርስቲ መምህር እና 'ፀጥታ እና ፍትህ ለትግራይ' በተሰኘው ተቋም ምክትል ፕሬዝዳንትየሆኑት ዶክተር ሙሉጌታ ገብረእግዚአብሄር በበኩላቸው ረቂቅ ህጉ ኢትዮጵያን ሊቀጣ ሳይሆን ኢትዮጵያን ሊያግዝ፣እንዲሁም ሀገሪቱ ወደ ሰላም እና ዲሞክራሲ እንድትሄድ የሚገፋፋ መሆኑን በመግለፅ ረቂቅ ህጉ መቅረቡ የሚደገፍ ነውይላሉ።
ዶክተር ሙሉጌታ አክለው ኢትዮጵያ የራሷን የውስጥ ችግሮች በራሷ መፍታት ቢኖርባትም መንግስት ግን ይህን ማድረግባለመቻሉ በዩናይትድ ስቴትስ የህግ አውጪና መወሰኛ ምክር ቤቶች እየቀረቡ እንዳሉት ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 አይነት ተመሳሳይ ረቂቅ ህጎች እንደአስገዳጅ ሁኔታ መቅረብ አለባቸውም ይላሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ያሉት ግጭቶች እንዲቆሙ ጫና ለማሳደር ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዕድገት ዕድል ድንጋጌ (አጎአ) በጊዜያዊነት እንድትታገድ ማድረጓን ተከትሎ ኢትዮጵያ በእገዳው ላይ ተቀምጠው የነበሩ በእስር ላይ ያሉ ሰዎችእንዲፈቱ፣ አስቸኳይ ግዜ እንዲነሳ እና ሌሎች ተያያዥ መስፈርቶችን በራስ ተነሽነት እያሟላች መሆኑንና የአጎአ እግድእንዲነሳ ከአሜሪካ ጋር እየተሰራ እንደሆነ የሚገልፁት አምባሳደር ፍፁም፣ በኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እና ጫናማሳደር ተገቢ አለመሆኑን በመግለፅ ሁኔታው በድጋሚ እንዲታይ ጥያቄ ማቅረባቸውን አስረድተዋል።
በዛሬው እለት በዩናይትድ ስቴትስ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጪ ግንኙነቶች ኮሚቴ እንዲታይና የምስክሮች አስተያየትእንዲደመጥ ቀጠሮ ተይዞለት በነበረው ሂደት ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን እያሰባሰብን ሲሆን በጉዳዩ ላይ ያለውን መረጃሰፋ ባለ ሁኔታ ይዘን የምንመለስ መሆኑን እንገልፃለን።