በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖሩ ሰባት ሕጻናት ተገደሉ


14 displaced people, including 7 children, killed in DR Congo
14 displaced people, including 7 children, killed in DR Congo

በሰሜን ምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአንድ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ሰባት ሕጻናት እና 14 ሲቪሎች መገደላቸውን የሃገሪቱ ቀይ መስቀል ዛሬ አስታወቀ፡፡

ሰባት አዋቂዎች እና የሁለት ዓመት ሕጻን ጨምሮ ሰባት ሕጻናት ኢቱሪ በተሰኘ የሃገሪቱ ክልል ውስጥ መገደላቸውን ቀይ መስቀል ጨምሮ አስታውቋል፡፡

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ የሚዘዋወሩት እና ሌንዱ ከተሰኘው የሚሊሺያ ቡድን ጋር ትስስር ያላቸው ኮዴኮ የተሰኙ የሚሊሺያ ቡድኖች 12 ሰዎችን በገጀራ መትተው መግደላቸውን የኢቱሪ ማኅበረሰብ መሪ የሆኑት ጂን ዲዜባ ባንጂ ገልጸዋል፡፡

ኮዴኮ በአካቢያዊ የሚዘዋወሩ እና ሌንዱ የተሰኘው ብሔር ቡድን የሚወክል የፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ክፍል ነው፡፡

XS
SM
MD
LG