በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ ተደጋጋሚ የሚሳይል ሙከራዎችን አደረገች

People watch a news program showing a file image of North Korea's rocket launch, at the Seoul Railway Station in Seoul, South Korea, March 20, 2022.
People watch a news program showing a file image of North Korea's rocket launch, at the Seoul Railway Station in Seoul, South Korea, March 20, 2022.

ሰሜን ኮሪያ የሮኬት ማስወንጨፊያዎችን በመጠቀም ተደጋጋሚ የሚሳይል ማስወንጨፎችን ፈጽማለች፡፡ ስትል ደቡብ ኮሪያ አስታወቀች፡፡

የደቡብ ኮሪያ መንግስት ያወጣው መገለጫ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን ነገር ግን የሚሳይሉን ክልል፣ አቅጣጫ እና ምን ዓይነት መሳሪያ እንደተወነጨፈ ዝርዝሩን አላስታወቀም፡፡

የደቡብ ኮሪያ የዜና አውታር የሆነው ዩን ሃብ የዜና ጣቢያ ሰሜን ኮሪያ በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ በደቡብ ኮሪያ ፒዮንግያንግ ግዛት ባለ የባሕር ወለል ላይ አራት ሚሳይሎችን ማስወንጨፏን ዘግቧል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለመምከርም የሲኦል የደህንነት ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን የዜና አውታሩ ጨምሮ አስታውቋል፡፡

እስካሁን ድረስም በዚህ በአዲሱ የአውሮፓዊያን ዓመት በሰሜን ኮሪያው መሪ ኮም ጁንግ ኡን ባለፈው ዓመት ባወጡት ስልታዊ የመሳሪያ ዕቅድ መሰረት ሃገሪቱ አስራ አንድ ዙር የሚሳይል ማስወንጨፎችን አካሂዳለች፡፡

XS
SM
MD
LG