በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘለንስኪ ከፑቲን ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነኝ አሉ


In this image from video provided by the Ukrainian Presidential Press Office, Ukrainian President Volodymyr Zelenskyy speaks from Kyiv, Ukraine, early Sunday, March 20, 2022. (Ukrainian Presidential Press Office via AP)
In this image from video provided by the Ukrainian Presidential Press Office, Ukrainian President Volodymyr Zelenskyy speaks from Kyiv, Ukraine, early Sunday, March 20, 2022. (Ukrainian Presidential Press Office via AP)

የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልድሚየር ዘለንስኪ ከፕሬዘዳንት ከብላድሚር ፑቲን ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ያሉ ሲሆን ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻልን “ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ይሆናል ማለት ነው” ብለዋል፡፡ ዘለንስኪ ከ ሲ.ኤን.ኤኑ የዜና ጣቢያ ጋዜጠኛ ፋሪድ ዛካሪያ ጋር ባደረጉት እና በዛሬው ዕለት በተላለፈው ቃለ መጠይቅ ላይ “ካለ ድርድር ይሄንን ጦርነት ልናስቆም አንችልም፡፡” ብለዋል፡፡

ዘለንስኪ ከሞስኮ ጋር የዩክሬንን ሉዓላዊነት የሚያስመለስ እና ፍትሕ የሚያሰፍን የተጠቃለለ የሰላም ንግግር ለማድረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የሩሲያ ዋና ተደራዳሪ በቅርብ ቀናት ባደረጉት ንግግር ዩክሬን የኔቶ አባል ሃገር መሆኗን በመተው ከወገንተኝነት የራቀ አካሄድ ልትከተል በመሆኑ ወደ ስምምነት እየደረስን ነው ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ዘለንስኪ “የሩሲያ ኃይሎች ወደ ዩክሬን የገቡት ሊያጠፉን ሊገድሉን ነው” ያሉ ሲሆን ነገር ግን ሉዓላዊነታችንን አይነኩብንም ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡

የሩሲያ ኃይሎች 400 ሲቪሎች የተጠለሉበት የስነ ጥበብ ት/ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት ፈጸሙ

የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ማሪፖል ከተማ 400 ሲቪሎች የተጠለሉበትን የስነ፟ጥበብ ትምህርት ቤት ላይ የቦንብ ጥቃት ፈጸሙ፡፡ የከተማው ምር ቤት በደረሰው የቦንብ ጥቃት ሕንጻው ሙሉ ለሙሉ መፍረሱን ያስታወቀ ሲሆን እስካሁን ድረስም ከጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተረፉ አልተገለጸም፡፡

የከተማው ም/ቤት በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማው ነዋሪዎች በጉልበት መወሰዳቸውን በትላንትናው ዕለት ባወጣው መገለጫ አስታውቋል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ኦልዲሚየር ዘለንስኪ በትላንትናው ዕለት በነበራቸው ማብራሪያ ሩሲያ በማሪፖል ከተማ ላይ እያደረሰች ያለቸው ጥቃት “በታሪክ ተጠያቂ የምትሆንበት የጦር ወንጀል ነው” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG