No media source currently available
ሰሞኑን ይፋ የተደረገው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በአማራ ክልል ከፍተኛ ቅሬታ አስነስቷል። ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆችና የትምሕርት ባለሞያዎች የፈተና ውጤቱ በሚገባ እንዳልታረመ ገልፀዋል። በክልሉ የነበረውን ወቅታዊ ችግርም ያገናዘበ እንዳልሆነ ተናግረዋል። የፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ችግሩ የተፈጠረው ሁለተኛ ዙር በተፈተኑ ተማሪዎች እንደሆነ ገልፀዋል። በጉዳዩም ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።