የደቡብ አፍሪካ የሕክምና ተማሪዎች የተቋረጠውን ትምሕርታቸውን የሚያጠናቅቁበትን መንገድ እየፈለጉ ነው። በሌላም በኩል የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ለተማሪዎቹ ያለውን አማራጭ እየተመለከቱ ነው። አንዳንዶቹ ተማሪዎች አሁንም ዩክሬን ውስጥ ያዩት ጥቃት ካሳደረሰባቸው ጭንቀት ገና አልወጡም ወደ ኋላ ትተዋቸው የወጡት መምሕራኖቻቸውና ጓደኞቻቸውም አሁንም ያሳስቧቸዋል፡፡
በቪኦኤ ሪፖርተሮች ከናይጄሪያ ቲሞቲ ኦቢዙ እና ከደቡብ አፍሪካ ቪኪ ስትራክ የተጠናቀሩትን ዘገባዎች ደረጀ ደስታ እንደሚከተለው ያቀርባቸዋል።