No media source currently available
በርካታ የአፍሪካ ሴቶች በእርሻ ሥራ ላይ የተሰማሩ ቢሆንም በሚያርሱት መሬት ላይ ሕጋዊ መብት ያላቸው ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው። ኬንያ ለምሳሌ ሴቶች የመሬት ባለቤትነት መብት እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ሕግ ቢኖራትም ሕጉን ወደተግባራዊነት ለመቀየር አስቸጋሪ ሆኗል። የሴቶችን የመሬት ባለቤትነት ለማስከበር የሚንቀሳቀስ አንድ ቡድን ግን ይህ ሁኔታ ለመቀየር እየተንቀሳቀሰ ነው።