የዋይት ሃውስ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ፕሬዚዳንት ባይደን በአፍሪካ ጉዳይ ላይ ያላቸውን ቁርጠኝነት ለማጽናት የታለመ መሆኑ በተነገረለት ዕቅድ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር ተወያዩ።
ሊቀመንበሩ ሙሳ ፋኪ እና ሚስተር ሱሊቫን እንደ አፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የመሳሰሉ ተቋማት ጨምሮ ዓለም የገጠሙ ፈተናዎች ለመጋፈጥ በትብብር ለመሥራት ተወያይተዋል።
ሚስተር ሱሊቫን አገራቸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት፣ ዓለም አቀፍ የጤና አጠባበቅ ግቦችን ማቀላጠፍ፤ ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ለመገንባት፣ የአየር ንብረት ቀውስን ለመታገል፣ ዲሞክራሲን ለማጎልበት እና የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን ማረጋገጥ በመሳሰሉት ሥራዎች ለስኬት ለመብቃት ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪቃ ጋር ተባብራ ለመስራት በቁርጥርኝነት መዘጋጀቷን አስታወሰዋል።
ሚስተር ሱሊቫን በተጨማሪም የወቅቱን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የሩስያ ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ህጎችን እና የዩክሬንን ብሄራዊ ሉዓላዊነት እንድታከብር ሲሉ ያሰሙትን” ጠንካራ ያሉትን መግለጫም አወድሰዋል።
የዋይት ሃውሱ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ፣ በማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ጊኒ ዲሞክራሲያን መልሶ መገንባት፣ በሱዳን እና በቻድ ያለውን የመሰለ በቋፍ ያለ የሽግግር ሂደት ለመደገፍ እና እንዲሁም ለኢትዮጵያ እና ለሶማሊያ ሰላማዊ እና የተረጋጋ መጭ ጊዜ መስራትን የመሳሰሉ አገራቸው እና አህጉራዊው ህብረት በጋራ ለመስራት ፍላጎት አላቸው ስላሏቸው ጉዳዮችም አውስተዋል።
በተያያዘ ርዕስ ፕሬዚዳንት ባይደን በያዝነው የአውሮፓውያኑ 2022 ዓመት ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ እና የአፍሪካ መሪዎች የተሰኘውና እና እንዲሁም የዓለም የኮቪድ-19 ጉባኤዎች የማስተናገድ ዕቅድ እንዳላቸው ተገልጧል።