በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፋር የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ


ፎቶ ፋይል፦ ሰመራ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ ሰመራ ከተማ
  • ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተላከው እርዳታ ወደ ትግራይ አለመድረሱን ክልሉ አስታወቀ

በአፋር ክልል በተከሰተው ጦርነት ምክኒያት የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። በመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽንን ጨምሮ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የአፋር አርብቶ አደሮች የልማት ማኅበር የተፈናቃዮቹ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰው ሕክምናን ጨምሮ አፋጣኝ ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የትግራይ ክልል የውጭ ጉዳዮች ቢሮ በጹሑፍ ባወጣው መግለጫ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት የተላከው ሰብዓዊ ረድኤት ወደ ክልሉ አለመድረሱን ገልፆ አፋር ክልልንና የፌደራል መንግሥቱን ተጠያቂ አድርጓል።

መሰረታዊ የሆኑ ሰብዓዊ ረድኤት የጫኑ መኪኖች ከዓለም አቀፍ የምግብ ፕሮግራም መነሳታቸውን ያሰፈረው መግለጫው፤ እስካሁን ትግራይ ክልል እንዳልደረሱ ለዚህ ደግሞ ተጠያቂው የአፋር ክልል መንግሥት መሆኑን ጽ/ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የጭነት መኪኖቹ ወደ ትግራይ ክልል እንዲጓዙ ፍቃድ ቢሰጣቸውም አፋር ክልል ውስጥ ተከልክለው መቆማቸው ኣሳዛኝ ድርጊት መሆኑን በመጥቀስ፤ “ውሳኔው ዜጎች ለሞትና ለረሃብ የሚያጋልጥ ነው” ብሎታል።

የሚመለከታቸው የክልሉ መንግሥት ተቋማት አመራሮች በሚነሱት ቅሬታዎችና በተፈናቃዮች ዙሪያ ምልሽ እንዲሰጡን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

በአፋር የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:14 0:00

XS
SM
MD
LG