የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሃገራቸው የምትገኝበትን ሁኔታ የሚተነትን ንግግር ዛሬ ያደርጋሉ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሃገራቸው የምትገኝበትን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያብራራ የመጀመሪያ ዓመታዊ ንግግራቸውን ለተወካዮች ምክር ቤቱ ጥምር ጉባዔ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ዛሬ ከምሽቱ ሦስት ሠዓት፤ በዓለምአቀፍ ሠዓት አቆጣጠር 0200 ጂኤቲ ወይም ለንደን ላይ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት፤ በአዲስ አበባ ጊዜ ከንጋቱ 11፡00 ሠዓት ላይ ያደርጋሉ። ፕሬዚዳንት ባይደን ያነሷቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ ጉዳዮች መካከል የሩሲያ የዩክሬን ወረራ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን፣ እንዲሁም የሃገራቸው ምጣኔ ኃብት ይገኙባቸዋል። ፕሬዚዳንት ባይደን ንግግራቸውን እንደጨረሱ የአዮዋ አገረ ገዥ ኪም ሬይኖልድስ የሪፐብሊካን ፓርቲውን ምላሽ ያሰማሉ።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ኦክቶበር 11, 2024
ትንታኔ:- ‘ሄሬኬን ሚልተን’
-
ኦክቶበር 11, 2024
በኢትዮጵያ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትግበራ ፍሬ እያፈራ ነው ተብሏል
-
ኦክቶበር 10, 2024
የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ከሚወስኑ የአሜሪካ ግዛቶች አንዱ የሆነው ዊስከንሰን
-
ኦክቶበር 10, 2024
የምርጫ ተዓማኒነት
-
ኦክቶበር 09, 2024
“ለፍልሰተኞች አስተማማኝና መደበኛ የእንቅስቃሴ መንገዶች ሊስፋፉ ይገባል” አይኦኤም
-
ኦክቶበር 07, 2024
ኢትዮጵያ አዲስ ፕሬዝዳንት ሰየመች