በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይ በሩሲያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ በመጣስ የተጠረጠረች መርከብ ያዘች።


የፈረንሳይ የባህር ጥበቃ ፖሊሶች ንብረትነቷ በሩስያ የዩክሬን ወረራ ሳቢያ የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ የተጣለበት አንድ የሩሲያ ኩባንያ ሳትሆን አትቀርም የተባለች መርከብ ዛሬ ቅዳሜ መያዛቸውን የፈረንሳይ ባለስልጣን ለሮይተርስ ተናገሩ።

ተሽከርካሪዎችን የምታጓጉዘው የጭነት መርከብ "ማዕቀቡ ከተነጣጠረበት አንድ የሩስያ ኩባንያ ጋር ግንኙነት አላት የሚል ከፍ ያለ ጥርጣሬ እንዳላቸው አንድ የፈረንሳይ የባህር ደሕነት ጥበቃ ሃላፊ ካፒቴን ቬሮኒክ ማግነን ተናገሩ።

ኃላፊዋ አክለውም መርከቢቱ ከጠዋቱ በአገሬው የሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ ዘጠኝ እስከ አሥር ሰዓት መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ነው በሰሜናዊ ፈረንሳይ ወደሚገኘው ቦሎኝ ሱር-መ ወደተባለ ወደብ እንድትመለስ መደረጉን እና የጉምሩክ ባለስልጣናት ቀጣይ ምርመራ እያካሄዱ መሆናቸውን አመልክተዋል። የመርከቢቱ ሰራኞችም ለፍተሻው መተባበራቸውን ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG