ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያደረገች ያለውን ወረራ ለማውገዝ እና ለማስቆም ትላንት አርብ ከተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ፊት የቀረበ ውሳኔ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ውድቅ አደረገች። ይሁንና በርካታ ሀገራት ሩስያን የመንግስታቱ ድርጅት አባል አገሮች በሙሉ በሚወከሉበት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተጠያቂ ማድረግ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ እና በአልባኒያ የረቀቀው የውሳኔ ሃሳብ ከ15ቱ የምክር ቤት አባላት የ11ዱን ድጋፍ ሲያገኝ፤ ቻይና፣ ህንድ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።