በአፋር ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክኒያት የፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ሙሳ አብዱላሂ እንደ አዲስ ባገረሸው ጦርነት ምክኒያት ሁለት ዳኞች መገደላቸውን፣ ሰነዶችና መዛግብት መውደምና መጥፋታቸውን ተናግረዋል። ለዚህም ህወሓትን ተጠያቂ አድርገዋል።
ስለ ሰነዶች መጓደልና የፍትሕ ሂደት የያዙ መዛግብት መጥፋትን ብተመለከተ ከህወሓት በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።
በሌላ በኩል የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት በአፋር ክልል ደርሷል ያሉትን ጉዳት በተመለከተ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እያሳወቅን ነው ብለዋል።