በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለማቀፉ የዜና አውታር ቢቢሲ ኢራንን በተመለከተ ለተመድ አቤቱታ አስገባ


ፋይል ፡ ሩሆላህ ዛም የተባለው ጋዜጠኛ ቴህራን የስለላ ኦፕሬሽን በተባለው ዘመቻ ተይዞ ኢራን ውስጥ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ሰኔ 2020 ችሎት በቀረበበት ወቅት
ፋይል ፡ ሩሆላህ ዛም የተባለው ጋዜጠኛ ቴህራን የስለላ ኦፕሬሽን በተባለው ዘመቻ ተይዞ ኢራን ውስጥ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ሰኔ 2020 ችሎት በቀረበበት ወቅት

ዓለም አቀፉ የዜና አውታር ቢቢሲ በፐርሺያ ቋንቋ ሠራተኞቹ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ኢራን ጥቃት እና ዛቻ እያደረሰች እንደሆነ ተናገረ። ቢቢሲ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባቀረበው ክስ ላይ ድርጅቱ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢራንን በሠራተኞቹ ላይ እየፈጸመች ያለችውን ተቀባይነት የሌለው አያያዝ እንዲያወግዙ ጠይቋል።

ቢቢሲ በክሱ ላይ ፤ "ኢራን በእንግሊዝ እና በሌሎች ሦስተኛ ሀገራት በሚኖሩ ጋዜጠኞች ላይ ድንበር ተሻጋሪ ስጋት ደቅናለች፣ በኢራን ውስጥ በሚኖሩ ቤተሰቦቻቸው ላይ እንግልት እና የፋይናንስ ጫና ትፈጽማለች፣ የቢቢሲ ፐርሺያ ቋንቋ ክፍል እና ጋዜጠኞች የሙያ ክብር ላይ ጉዳት ለማድረስ የስለላ ተግባራትን አስፋፍታለች" ብሏል ።

ችግሩ ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑን የተናገሩት የቢቢሲ ፐርሺየ የለንደን ልዩ ዘጋቢ ካስራ ናጂ ስጋቶቹ ግን በቅርቡ በእጅጉ እንዳየሉ አስታውቀዋል ።

ናጂ አክለው "ለወላጆቻችን፣ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ለንደን የምንገኝ ጋዜጠኞች ለቢቢሲ መሥራታችንን የምንቀጥል ከሆነ ልንታፈን ወይም ልንገደል እንደምንችል ነግረዋቸዋል" ብለዋል። ታፍነውም ለኢራን ሊሰጡ እንደሚችሉ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።

ጋዜጠኞቹ የተባሉትን የማያከብሩ ከሆነ እንደ ሩሆላህ ዛም ዓየንት ጉዳይ ሊፈጠር እንደሚችል ጠቅሰው እንዳስፈራሯቸውን ናጂ ተናግረዋል።

ሩሆላህ ዛም ፓሪስ ውስጥ በስደት በነበረበት ጊዜ መንግሥትን የሚቃወም ድረ ገጽና የቴሌግራም ቻናል ከፍቶ ይሠራ የነበረ ሲሆን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2019 ዓ.ም አንድ የኃይማኖት አባት ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ወደ ተያዘለት ቦታ ሲሄድ በቃለ ምልልሱ ፋንታ ታፍኖ ወደ ኢራን ተወስዶ ክስ የተመሰረተበት ጋዜጠኛ ነው።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢራን ተወካይ ከቪኦኤ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል ።

XS
SM
MD
LG