አማራ ክልል ውስጥ አሁንም በህወሃት ቁጥጥር ሥር ናቸው ከሚባሉት አካባቢዎች አንዱ ከሆነው ዋግ ኅምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የተለያዩ ወረዳና ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ከ35 ሽህ በላይ ሰዎች በመጠለያ ጣቢዎች እንደሚገኙ ተገልጿል።
ተፈናቃዮቹ ከፍተኛ የምግብና የመጠለያ ችግር እንዳለባቸው ለአሜሪካ ድምፅ አሳውቀዋል።
የተፈናቃዩ ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን የሚናገረው የዞኑ አስተዳደር ፌዴራል መንግሥቱና ዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ እንዲደርሱላቸው ጠይቋል።