በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፋር ተፈናቃዮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አንድ የአርብቶ አደሮች ድርጅት አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ ሰመራ፣ አፋር
ፎቶ ፋይል፦ ሰመራ፣ አፋር

የህወሓት ኃይሎች አድርሰውታል በተባለው ወታደራዊ ጥቃት ምክንያት አፋር ውስጥ የደረሰውን ሰብዓዊ ቀውስ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሚዛናዊነት አላየውም ሲል የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገልጿል።

የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳየች ጽ/ቤት ኃላፊ አህመድ ኮሎይታ በጥቃቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እና የመድኃኒት ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል።

በአፋር የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙት የኅብረተሰብ ክፍሎች የምግብና የሕክምና ድጋፍ በመስጠት ላይ የሚገኘው የአፋር አርብቶ አደሮች ማኅበር አስተባባሪ ቫለሪን ብራውኒንግ ተፈናቃዮቹ ያሉበትን ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ገልፀዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

የአፋር ተፈናቃዮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አንድ የአርብቶ አደሮች ድርጅት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:41 0:00

XS
SM
MD
LG