በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሆንግ ኮንግ ከንቲባ ከተማቸው በኦሚክሮን ተጋላጮች ተጨናንቃለች አሉ


በሆንግ ኮንግ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ ወረፋ ይዘው፤ እአአ ፌብሩዋሪ 12/2022
በሆንግ ኮንግ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ ወረፋ ይዘው፤ እአአ ፌብሩዋሪ 12/2022

በሆንግ ኮንግ በእጅጉ እያየለ የመጣው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መዛመት ወረርሽኙን ለመግታት የወጣውን እና "ዜሮ-ኮቪድ" የተሰኘውን የከተማይቱን ጥብቅ ፖሊሲ እያቃወሰ ባለበት፣ የጤና ተቋማት ከአቅማቸው በላይ በሕሙማን መጨናነቃቸውን የከተማይቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።

የቤጂንግ የጤና ባለስልጣናት ኮቪድ-19 ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ማዕከላዊ ቻይና የምታራምደውን እና አነስተኛ ወረርሽኝም ቢሆን በአንድ አካባቢ በታየ ጊዜ በፍጥነት ለቫይረሱ የተጋለጡትን በሙሉ በጅምላ ወደ ለይቶ ማቆያ በማስገበት መጠነ ሰፊ ክትትል እና የተራዘመ የማህበራዊ ርቀት እርምጃዎችን የመውሰድ አሰራር አሁንም ድረስ ተፈጻሚ እንዳደረጉ ነው።

ይሁንና በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ባለውው የአምስተኛው የወረርሽኙ ማዕበል፣ በተለይ በስፋት የታየው የኦሚክሮን ዝርያ በጥቂት ሳምንታት ዕድሜ ከ8 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጋላጭ በማድረግ፤ ካለፈው የታህሳስ ወር አጋማሽ ግድም አንስቶ ቻይና ያዋቀረችውን ጥብቅ የመከላከያ አሰራር መገርሰስ መገርሰስ መያዙ ተዘግቧል። እስከአሁን የታየው አሃዝ በሚቀጥለው ወር ከ25 ሺህ ሊልቅ እንደሚችልም ባለሞያዎች አስጠንቅቀዋል።

ለወረርሽኙ የሚጋለጠው ሰው ቁጥር በአጠቃላይ በዓለም ዙሪያ ካሉ ዋና ዋና ከተሞች ጋር ሲነጻጸር አሁንም ዝቅተኛ ቢሆንም፣ ምንም ምልክት የሌላቸውን ጨምሮ ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎችን በሙሉ ወደ ሆስፒታሎች እና የለይቶ ማቆያ ተቋማት በመላክ ሆንግ ኮንግ የምትከተለው ፖሊሲ በሕክምና መስጫ ተቋማቱም ሆነ ለይቶ ማቆያ ማዕከሎች መኝታዎች ከመሙላታቸውም በላይ፣ ሰዎች ተራ ለማግኘት የሚጠባበቁት የጊዜ መጠን እንዲራዘም ማስገደዱ ተመልክቷል።

ሙሉውን ባለፈው ሳምንት የጤና ምርመራ ለማድረግ ተራ በመጠባበቅ ላይ በነበሩ ህሙማን ዙሪያቸውን ተከበው የሰነበቱት የከተማይቱ ሆስፒታሎች፣ ትላንት እሁድ “የተረጋጋ ወይም ቀላል የሕመም ምልክት ያላቸው” ሰዎች ከቤታቸው እንዲቆዩ ለመጠየቅ ተገደዋል።

ሆኖም የከተማይቱ አስተዳዳሪ ኬሪ ላም መንግስት ምንግዜም "ዜሮ ኮቪድ" የተሰኘውን ጥብቅ ደምብ ተግባራዊነት ሳያረጋገጥ የሚያጠፋው ጊዜ አይኖርም” ብለዋል። “የከተማዋን የምርመራ እና የለይቶ ማቆያ ተቋማት ለማጠናከር የሚያስችል ድጋፍ ከቻይና ይመጣል።” ሲሉም ተደምጠዋል።

እድሜያቸው ከ70 በላይ ከሆኑ ዜጎቿ መካከል 50 በመቶው ብቻ በተከተቡባት ሆንግ ኮንግ ለቫይረሱ ከተጋለጡ ይበልጥ የመጎዳት ዕጣ የሚገጥማቸው አረጋውያንን ሙሉ በሙሉ እንዲከተቡ ለማሳመን አሁንም ገና ጥረት በማድረግ ላይ ነች።

XS
SM
MD
LG