በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን የጦርነት ሥጋት በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ የአክሲዮን ገበያዎች መዋዥቅ አስከተለ


ፎቶው በሆንግ ኮንግ የአክሲዮን ልውውጥ ግብይት ሁኔታን ያሳያል፤ እአአ ፌብሩዋሪ 14/2022
ፎቶው በሆንግ ኮንግ የአክሲዮን ልውውጥ ግብይት ሁኔታን ያሳያል፤ እአአ ፌብሩዋሪ 14/2022

“ሩሲያ በማንኛውም ጊዜ ዩክሬንን ልትወር ትችላለች” የሚለውን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ፣ በዓለም ዙሪያ የአክሲዮን ገበያዎች ከፍተኛ መዋዠቅ ታይቶባቸዋል።

የዩሮ የምንዛሪ ዋጋ በመውረዱ፣ ኢንቨስተሮች ዓመቱን በሙሉ ገሸሽ አድርገው ወደነበሯቸው እና እምብዛም ወዋዥቅ ወደማይታይባቸው የመንግስት ቦንዶች በጥድፊያ ፊታቸውን ሲያዞሩም ተስተውለዋል።

ስታክስ 600 በመባል የሚታወቀው የአውሮፓ አክሲዮን በ2 ነጥብ 5 በመቶ፣ የጃፓን ኒኬ ደግሞ በአንድ ለሊት አዳር በ2 ነጥብ 2 ሲቀንስ፤ የዩክሬን የቦንድ ዋጋ በ10 በመቶ አሽቆልቁሏል።

ባለፉት 7 ዓመታት ውስጥ ከታዩት ሁሉ ከፍተኛውን ደረጃ የያዘው የድፍድፍ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በአንጻሩ የአንድ በርሜል ዋጋ 95 ዶላር በላይ ጨምሮ ታይቷል።

"የሩሲያ ወረራ ከተከሰተ፣ ጥያቄው በምን መልኩ ይደረጋል?" የሚለው ነው ያሉት አክሳ የኢንቨስትመንት ስራ አስኪያጆች መድረክ በተሰኘው ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ድርጅት የኢንቨስትመንት ባለሞያ ጂም ቬኑ ናቸው። ጦርነቱ በተለመደው በታንኮች የተመራ የሜካናይዝድ ጦር ወይንስ በሳይበር ጥቃት የታገዘ ቅይጥ ወታደራዊ ኦፕሬሽን?

በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን የተማረነው አሳሳቢ ነገር ግን “ሩሲያን እና ኔቶን የሚመለከት ማንኛውም ሁኔታ የኑክሌር መሳሪያ ፉክክር ውስጥ ሊገባ ይችላል” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG