በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቄለም ወለጋ ጊዳም ወረዳ የጅምላ አስክሬን መገኘቱን ዞኑ አስታወቀ


የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የፈረጀውና መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራው የታጠቀ ቡድን የኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳን ተቆጣጥሮ በቆየበት ወቅት ግድያ የተፈፀመባቸው ሰዎች የጅምላ አስክሬን መገኘቱን የዞን አስተዳደር ተወካይ እና የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሣ በሻ አስታወቁ።

በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርጊቱን የፈፀሙ ሰዎች ለሕግ እንዲቀርቡና ለተጎጂዎችም ካሳ እንዲከፈል ጠይቀዋል። የክልሉ ፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ወረዳዋ በአሁኑ ሰዓት ከታጣቂዎቹ ነፃ ሆናለች ብሏል።

የቄለም ወለጋ ጽ/ቤ በኩሉ 80 የሚሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ታግተው እንደሚገኙ አስታውቋል። የአሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ ድርጊቱን አስተባብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በቄለም ወለጋ ጊዳም ወረዳ የጅምላ አስክሬን መገኘቱን ዞኑ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:48 0:00



XS
SM
MD
LG