በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ፌስቲቫል እንደሆነ የሚነገርለት ታላቁ ሩጫ ለ21ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ባካሄደው ውድድር ላይ በጀመረው የአረንጓዴ ዘመቻ ከ 350 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን ደረቅ ቆሻሻ ተሰብስቦ እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረጉን አስታውቋል። በ21 አመታት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አረንጓዴ ዘመቻን የተቀላቀለው ታላቁ ሩጫ በቀጣይ በሀገሪቱ ላይ የሚያካሂዳቸው ውድድሮች የአካባቢ ጥበቃን ታሳቢ ያደረጉና የህብረተሰቡን ግንዛቤ የሚያሰፉ መሆናቸውንም ገልጿል። ስመኝሽ የቆየ በታላቁ ሩጫ ስለተከናወነው የአረንጓዴ ዘመቻና ጅማሮው ያመጣው ውጤት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የኦፕሬሽን ዳይሬክተር ዳግም ተሾመ ጋር ቆይታ አድርጋለች።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ጁላይ 26, 2024
የኢትዮጵያውያኑ ባህላዊ ማዕድ እና አብሮነት ታዛ - በሚልዋኪ
-
ጁላይ 26, 2024
የፕሬዝደንት ጆ ባይደን ንግግር
-
ጁላይ 23, 2024
አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በኮዲንግ ሞያ የማብቃት መርሐ ግብር ይፋ ኾነ
-
ጁላይ 22, 2024
የነዋሪዎች አስተያየት በፕሬዝደንት ባይደን ውሳኔ ላይ
-
ጁላይ 18, 2024
ጄ. ዲ. ቫንስ “አሜሪካ ትቅደም” መሪ ቃላቸው እንደሆነ አስታወቁ