በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ የዳርፉር አማጽያን አሁንም በሊቢያ ገንዘብ እየሰሩ ነው አለ


.
.

የተባበሩት መንግሥታት ባለሙያዎች እኤአ በ2020 ከሱዳን መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረሙት የዳርፉር አማጽያን ቡድኖች፣ አሁን ድረስ በሊቢያ ያደርጉ የነበሩትን እንቅስቃሴ አለማቋረጣቸውን አስታወቁ፡፡

አማጽያኑ በሊቢያ የተፈጠረውን የርስ በርስ ጦርነትና የመንግስት ቁጥጥር አለመኖር አጋጣሚን ተጠቅመው፣ በነዳጅ በበለጸገችው አፍሪካዊቷ አገር በመንቀሳቀስ ገንዘብ እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣናት ኤክሰፐርቶች፣ አማጽያኑ በሊቢያ የሚያገኟቸው በርካታ ጥቅሞች ስላሉ ከዚያ ለቀው መውጣት የማይፈልጉ መሆኑን ፣ ከበርካታ አማጽያን ምንጮች መገንዘባቸውን አመልክተዋል፡፡

በዳርፉ ካሉ ትላልቅ የአማጽያን ቡድኖች መካከል አንዱ፣ ከፕሬዚዳንት አልበሽር ውድቀት በኋላ፣ በሱዳን የወታደራዊና ሲቪል ጥምር የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጁባ ላይ በተደረሰው ስምምነት ውስጥ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልነበረ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የሱዳን መንግሥት ትናንት ባወጣው መግለጫ ደግሞ በዳርፉር ከተሞች የሚገኙ የተለያዩ ታጣቂዎችና አማጽያን ቡድኖች ከተሞችን ለቀው እንዲወጡና ከተሞቹ ከመንግሥትና ከአማጽያን በተውጣጡ ኃይሎች እንዲጠበቁ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG