በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮምያ ፖሊስ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽኑን ግኝቶች ተቀበለ


የኦሮምያ ፖሊስ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽኑን ግኝቶች ተቀበለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:16 0:00

በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ውስጥ በከረዩ ሚችሌ ገዳ አባላት ላይ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ ሁለት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ ያሠፈረውን ግኝት እንደሚቀበሉና ምርመራ ለመክፈት የሚያስችሉ መነሻ ጭብጦችን ፖሊስ ማግኘቱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ትናንት (ረቡዕ) ባወጣው ሪፖርቱ በተጠቀሰው አካባቢ “በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከህግ አግባብ ውጭ የሆኑ ግድያዎች ስለመፈፀማቸው ምክንያታዊ አሳማኝ ሁኔታ መኖሩን” ጠቅሶ ግድያዎቹን የፈፀሙና ያስፈፀሙ፣ የፖሊስ አባላትን የገደሉና የአካል ጉዳት ያደረሱ ሰዎች በተጠያቂነት እንዲያዙ አሳስቦ ነበር።

XS
SM
MD
LG