በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል ሥራ እንዲፋጠን የአፍሪካ ሚኒስትሮች ወሰኑ


የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል ሥራ እንዲፋጠን የአፍሪካ ሚኒስትሮች ወሰኑ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:25 0:00

የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት በዛሬውየሁለተኛ ቀን ውሎው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ስለመቆጣጠርናበሌሎችም አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በዝግ ተወያይቷል። ምክር ቤቱ አዲስ አበባ ውስጥ እየተገነባ የሚገኘው የአፍሪካየበሽታዎች መቆጣጠርያና መከላከያ ማዕከል በፍጥነት ወደ ሥራእንዲገባ መወሰኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት በዛሬው የሁለተኛ ቀን ውሎው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ስለመቆጣጠርና በሌሎችም አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በዝግ ተወያይቷል።
ምክር ቤቱ አዲስ አበባ ውስጥ እየተገነባ የሚገኘው የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠርያና መከላከያ ማዕከል በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቱኒዚያ እና ከሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ከጉባዔው ጎን ለጎን በተናጠል መወያየታቸውንና ከአባይ ውኃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ሃገሮቹና የአረብ ሊግ ያራምዷቸዋል ያሏቸውን አቋም እንዲመረምሩና እንዲያስተካክሉ መጠየቃቸውንም ቃል አቀባዩ አመልክተዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪድዮ ዘገባ ያገኛሉ።)

XS
SM
MD
LG