በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት ተቆጣጥሯቸዋል በተባሉ የአፋር ከተሞች እርዳታ ማድረስ እንዳልቻለ ክልሉ አስታወቀ


map of Ethiopia
map of Ethiopia

የህወሓት ኃይሎች አፋር ክልል ውስጥ ከፈቱት በተባለው ወታደራዊ ጥቃት ምክንያት ተፈናቅለው ከአካባቢያቸው ለወጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በቂ ሰብአዊ እርዳታ ማድረስ አለመቻሉን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መሐመድ ሃሰን ከ290 ሽህ የሚልቁ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጸው የህወሓት ኃይሎች ዘልቀው ገብተውባቸዋል ባሏቸው አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን መድረስ አለመቻሉንም ገልጸዋል፡፡

የአፋር ሰብአዊ መብቶቸ ድርጅት በበኩሉ የህወሓት ኃይሎች በአካባቢው የቀጠሉት ወታደራዊ ጥቃት አገራዊ መረጋጋት እንዳይኖርና በህዝቦች መካከል የማይሽር ቂም እንዲፈጠር ያደርጋል ሲል ስጋቱን ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴ፣ በረድዔት አቅርቦት ችግር ምክንያት ሊቋረጥ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅዳሜ ዕለት አስታውቋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራምም ጦርነቱ 40 በመቶ የሚሆነው የትግራይን ሕዝብ ለርሃብ ዳርጎታል ብሏል።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ህወሓት ተቆጣጥሯቸዋል በተባሉ የአፋር ከተሞች እርዳታ ማድረስ እንዳልቻለ ክልሉ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:11 0:00


XS
SM
MD
LG