በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዋሽንግተን አካባቢ አብያተ ክርስቲያናት ለተጎጂዎች 300ሺ ዶላር ላኩ


የዋሽንግተን አካባቢ አብያተ ክርስቲያናት ለተጎጂዎች 300ሺ ዶላር ላኩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:12 0:00

በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተንና አካባቢው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገረ ስብከት ስር ያሉ ምዕመናንና ቤተክርስቲያናት በኢትዮጵያ ባለው ጦርነት ተጎጂ ለሆኑ በአፋርና አማራ ክልል ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከ300ሺ ዶላር በላይ መላካቸውን አስታወቁ፡፡

“ይህ በአይዞን በኩል አንድ ላይ በህብራት እንዲላክ በሚል ነው እንጂ ቤተክርስቲያናቱ ከዚያ በፊት ለየብቻቸው የላኩት ከ500ሺ ዶላር በላይ ይደርሳል” ሲሉም በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
በኮቪድ-19 የተነሳ ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጣው ምዕመን ባይቀንስ ኖሮ ከዚያም በላይ ሊላክ የሚችል መሆኑንም አቡነ ፋኑኤል ገልጸዋል፡፡
ዕርዳታውን ባለፈው ቅዳሜ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቀርበው ለአምባሳደር ፍጽም አረጋ ያስረከቡት አቡነ ፋኑኤል እርዳታውን ወደ ኢትዮጵያ የላኩትን 10 አብያተ ክርስቲያናትን ዝርዝር ከለገሱት የገንዘብ መጠን ጋር በመግለጽ አመስግነዋል፡፡
XS
SM
MD
LG