በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦሚክሮንን ለመከላከል ባይደን የፊት መሸፈኛ ጭምብልና የቤት ውስጥ መመርመሪያ በነፃ ለማሰራጨት ቃል ገቡ


ኦሚክሮንን ለመከላከል ባይደን የፊት መሸፈኛ ጭምብልና የቤት ውስጥ መመርመሪያ በነፃ ለማሰራጨት ቃል ገቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:33 0:00

በዩናይትድ ስቴትስ በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ በሆነው ኦሚክሮን የኮሮናቫይረስ ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨምረ ባለበት ወቅት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እና በቢሊየን የሚቆጠር የቤት ውስጥ መመርመሪያ መሳሪያዎችን በነፃ በማሰራጨት ወረርሽኙን የመዋጋት ጥረታቸውን ማጠናከራቸውን አስታውቀዋል።

ሆኖም ለጤና እኩልነት የሚከራከሩ ቡድኖች የአንድን ሀገር የመከላከል አቅም ብቻ በማጠናከር ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ማስቆም እንደማይቻልና፣ ቀሪው ዓለምም እርዳታ እንደሚፈልግ እየተናገሩ ነው።
የዋይት ኃውስ ዘጋቢያችን አኒታ ፓውል ከዋሽንግተን ዲሲ ያደረሰችንን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።
XS
SM
MD
LG