በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያው ፕሬዘዳንት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማገድ ስልጣን አላቸውን?

FILE - Somali President Mohamed Abdullahi Farmajo attends the London Somalia Conference' at Lancaster House, May 11, 2017.
FILE - Somali President Mohamed Abdullahi Farmajo attends the London Somalia Conference' at Lancaster House, May 11, 2017.

የሶማሊያው ፕረዘዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብሌ በሶማሊያ እየተካሄደ ያለውን ምርጫ በመመሪያው መሰረት እንዲካሄድ እያደረጉ አይደለም በማለት ስልጣናቸውን ማገዳቸውን ተከትሎ በሶማሊያ ፖለቲካዊ ውጥረት ነግሷል፡፡ የሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ/ ፎርማጆ የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ስልጣን ማገዳቸውን ሕገመንግስታዊ ነው ወይ የሚለው ሃሳብም አከራካሪ ሆኗል፡፡

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሁለቱ መሪዎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ጥሪ እያቀረበ ሲሆን በጉዳዩ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት መግለጫ አውጥቷል፡፡ በሶማሊያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣት ትውልደ ሶማሊያዊት የሚኒሶታ ግዛት የምክርቤት አባል ኢልሃን ኦማርም ትላንት ምሽት በትዊተር ገጿ ላይ የሶማሊያው ፕረዘዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ የስልጣን ዘመን ካበቃ ቆየ ፕሬዘዳንት ገለል ሊሉ ይገባል ስትል ድጋፏን ለጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብሌ አሳይታለች፡፡

የሶማሊያው ፕሬዘዳንት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማገድ ስልጣን አላቸውን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:41 0:00

XS
SM
MD
LG