በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራና በአፋር ክልል የደረሱት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ከፍተኛ መሆናቸውን መንግሥት አስታወቀ


በአማራና በአፋር ክልል የደረሱት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ከፍተኛ መሆናቸውን መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:37 0:00

በአማራና በአፋር ክልል የደረሱት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ከፍተኛ መሆናቸውን መንግሥት አስታወቀ

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀውና ራሱን የትግራይ ሠራዊት እያለ የሚጠራው አካል ይዟቸው በነበሩት የአማራና የአፋር ክልል ከተሞች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ፈፅሞ መሄዱንና የንብረት ውድመት መድረሱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ መሆኑንና እየተጣራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትም የደረሱት ጥፋቶች እንዲያጣሩ መንግሥት ጥሪ ማቅረቡን ገልፀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ በሰሜን ኢትዮጵያ በረሃብ ለተጎዱ ሰዎች ለማዳረስ ያስቀመጠው ከፍተኛ መጠን ያለው ምግብ ከእህል መጋዘኖቹ በትግራይ ተዋጊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች መዘረፉን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ አምባሳደር ታየ አፅቀሥላሴ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት በኮምቦልቻ የሚገኙት የእርዳታ እህል መጋዘኖች በህወሓት ታጣቂዎች ሆን ተብለው መዘረፋቸው ትክክል ሆኖ ሳለ የአካባቢውን ማኅበረሰብ መወንጀል ግን ጥፋተኝነቱን የጥቃት ሰለባዎች ላይ ማላከክ ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

XS
SM
MD
LG