በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግስት ደሴና ኮምቦልቻን ነፃ ማውጣቱን አስታወቀ


የኢትዮጵያ መንግስት ደሴና ኮምቦልቻን ነፃ ማውጣቱን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:22 0:00

የአማጺው የትግራይ ኋይሎች ተቆጣጥረዋቸው የነበሩትና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ተንታኞች "ቁልፍ" ስፍራ ናቸው የተባሉት ደሴና ኮምቦልቻን የኢትዮጵያ መንግሥት ነፃ ማውጣቱን ማምሻውን አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል የሚገኙት ደሴ እና ኮምቦልቻን እንዲሁም ባቲን ጨምሮ በምስራቅ ግንባር የሚገኙ በርካታ ከተሞች በኢትዮጵያ በመንግስት የጸጥታ ኋይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።

ከጥቅምት ወር ጀምሮ በአማጽያኑ የትግራይ ኋይሎች ቁጥጥር ስር የነበሩትና በዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት እናተንታኞች ለጦር አሰላለፍ ቁልፍ መሆናቸው ሲነገር የቆየው ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይአህመድ የተመራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ነፃ መውጣታቸውን የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ዛሬአስታውቋል።

ታሪካዊ ከተማ ከሆነችው ደሴ እና በንግድ እና ኢንዱስትሪ ኮሪደርነቷ ከምትታወቀው ኮምቦልቻ በተጨማሪም የኢዮጵያመንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው እንዲሁም እራሳቸውን የትግራይ ሰራዊት ብለው በሚጠሩት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስርየነበሩ፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞን የምትገኘው የባቲ ከተማ ፣ቀርሳ፣ ገርባና ደርጋን ከተሞችን የኢትዮጵያ ሰራዊት ነፃ ማውጣቱንየኮሚዩኒኬሽን ቢሮው ገልጿል። በሌላ በኩል ደግሞ በሐርቡ ግንባር ቃሉ ወረዳን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩንመግለጫው ጨምሮ አስታውቋል።

ከዛሬ በፊት በነበሩት ቀናት ታሪካዊቷን የላሊበላ ከተማ እና ጋሸናን ነፃ ማውጣቱን የኢትዮጵያ መንግስት ገልጾ የነበረሲሆን በነዚህ ቦታዎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈፀማቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንአስታውቋል። በተጨማሪም በላሊበላ የውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን እስካሁን በውልአለመታወቁን ሆኖም ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን ለታሪካዊ ቅርሱ አስፈላጊውን ጥገና ለማድረግ ጋር ዝግጅትመጀመሩን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

ይህን ተከትሎ የትግራይ ክልል መንግስት አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር የማህበራዊ ትስስር ገፃቸውባሰፈሩት መልዕክት የትግራይ አማፂያን ቡድኑ ይዟቸው በነበሩ ግዛቶች ላይ ማስተካከያ እያደረገ መሆኑንና ቀጣዩርምጃቸው ስልታዊ ክንዋኔዎችን ያገናዘበ እንደሆነ አስታውቀዋል። የውሳኔያቸው አላማ በዋናነት የህዝባቸውን ደህነትማስጠበቅ መሆኑን የገለፁት አቶ ጌታቸው በመጪው ሳምንታት ውጤት የሚያስገኝላቸው ሁኔታ ላይ እንደሚደርሱተናግረዋል። አቶ ጌታቸው ጨምረው ከጣርማ በር እስከ ደሴ ባሉ ውጊያዎች ጠላትን ማሸነፋቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው በጥቅምት ወር ከተሞቹን መቆጣጠራቸውን ለሮይተርስ በተናገሩበት ወቅት አማጺያኑ ከፌደራል መንግስቱጋር እያደረጉት ባለው ውጊያና ወደ አዲስ አበባ በሚያደርጉት ግስጋሴ ስልታዊ ድል መሆኑ ተገልጾ ነበር።

XS
SM
MD
LG