ዋሽንግተን ዲሲ —
ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የታየው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ኦሚክሮን በተለያዩ የዓለም አካባቢዎች እየታየ ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዋና የጤና አማካሪ አንተኒ ፋውቺ ኦሚክሮን ከሌሎቹ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች የበለጠ ተላላፊ መሆኑን ቢገልፁም የጤና ባለሙያዎች ግን “የበለጠ ህመም ያስከትል ይሆን ወይ?” ለሚለው እርግጠኛ አይደሉም።
በሌላ በኩል ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከቤት ያለመውጣት ጠንካራ ክልከላ የተላለፈ ሲሆን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖሳ “ክትባቱን ላልወሰዱ ሰዎች መከተቢያው ሰዓት አሁን ነው” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
[ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ።]